አራቱ መንገደኞች
አራቱም መንገደኞች ወደ ኢመራልድ ከተማ ታላቁ
በር አመሩ፤ ደውሉንም ደወሉ፡፡ ከብዙ ደውሎች በኃላ ከዚህ ቀደም በሚያውቁት ጠባቂ ተከፈተላቸው፡፡
“ ምን ! በድጋሚ ተመለሳችሁ ?” በግርምት ጠየቀ፡፡
“ አንታይህም እንዴ ?” ወፍ ማስፈራሪያው መለሰ፡፡
“የምዕራቧን እርጉም ጠንቋይ ልታይዋት የሄዳችሁ መስሎኝ፡፡”
“አዎ ጎብኝተናት ነበር፣ አለ ወፍ ማስፈራሪያው ”
“እና በድጋሚ ለቀቀቻችሁ ? ” ሰውዬው በመገረም ጠየቀ፡፡
“በመቅለጧ ምንም ልታደርግ አትችልም ” በማለት ወፍ ማስፈራሪው አስረዳ፡፡
“ ቀለጠች !” መልካም፣ በእርግጥ ይህ በጣም ጥሩ ዜና ነው አለ ሰውዬው
፡፡ “ማነው ያቀለጣት?”
“ዶርቲ ነች” አለ አንበሳው ደረቱን ነፍቶ::
“በጣም አስደሳች! ” ሰውየው በመደነቅ ይህን
ካለ በኃላ በፊቷ እጅ ነሳ::
ከዚያም ወደ ትንሿ ክፍል ካስገባቸው በኃላ ከዚህ
በፊት እንደሚያደርገው ሁሉ ከታላቁ ሳጥን ውስጥ መነፅሮችን አረገላቸው፡፡
በመቀጠል በሩን አቋርጠው ወደ ኤመራልድ ከተማ ዘለቁ፡፡
ህዝቡ የዶርቲን ጀግንነት ከጠባቂው
ሲሰሙ ወደ እነርሱ በመጠጋት በታላቅ አጀብ ወደ ኦዝ ቤተመ
የጠባቂዎቹን ድምፅ መግቢያው
ላይ ሲሰሙ ወደ ኦዝ ቤተመንግስት ወሰዷቸው፡፡
ባለ አረንጓዴ ጢማም ወታደር
አሁንም ከመግቢያው ፊት ተገትሯል ፤ ሆኖም አራቱንም ወደ ውስጥ አስገባቸው፡፡
እዛም አረንጓዴ መልከ መልካምዋን
ልጅ በድጋሚ አገኙዋት፤ ታላቁ ኦዝ ተቀብሎ እስኪያስተናግዳቸውም በዚያ እንዲያርፉ ለሁሉም ማረፊያ በተዘጋጀውን ከዚህ ቀደም ያረፉበትን
ክፍሎች አሳየቻቸው፡፡
ወታደሩ ዶርቲ እና ሌሎቹ ተጓዦች
ዕርጉሟን ጠንቋይ አጥፍተው የመመለሳቸውን ዜና በቀጥታ ለኦዝ አበሰረው፤እርሱ ግን ምንም ምላሽ አልሰጠውም፡፡
እነርሱም ታላቁ ጥበበኛ አፋጣኝ
መልስ እንደሚሰጣቸው አስበው ነበር ነገር ግን ሳያደርገው ቀረ፡፡ ለተከታታይ ሶስት ቀናት አንዳች ምላሽ ሳያገኙ ቀሩ፡፡
ጥበቃው በጣም አሰልቺና አድካሚ
ነበር ፡፡
በመጨረቫም ኦዝ ለግዞተኝነት
እና ለባርነት ዳርጓቸው እንኳን አስደሳች አቀባበል ባለማድረጉ እጅግ ተበሳጩ፡፡
ወፍ ማስፈራሪያው ኦዝ አንዴ
እንኳን እንዲገናኛቸው የማይፈቅድ ከሆነ ክንፋም ጦጣዎችን ለእርዳታ እንደሚጠሯቸው እንዲሁም የገባውን ቃል መፈፀም እና አለመፈፀሙን
እንድታረጋግጥላቸው እና መልዕክቱንም ከታላቁ ጥበበኛ ዘንድ ታደርስላቸው ዘንድ ጠየቃት፡፡
ኦዝ ይህ መልዕክት እንደደረሰው
በጣም ስለፈራ ከጠዋቱ3፡04 ደቂቃ ላይ በዙፋኑ ሆኖ እንደሚያገኛቸው መልሶ መልዕክት ላከባቸው፡፡ክንፋም ጦጣዎቹን በምዕራብ ምድር
ላይ አንዴ ስላገኛቸው ደግሞ ሊያያቸው አይመኝም፡፡
አራቱ መንገደኞች ያለ እንቅልፍ
ሌሊቱን አሳለፉ
ሁሉም ኦዝ ሊሰጣቸው ቃል ስለገባላቸው
ስጦታ ያስቡ ነበር ዶርቲ ግን አንዴ ሸለብ ቢያደርጋት በህልሟ ካንሳስ ከተማ ውስጥ በአክስቷ ኢም እቅፍ ውስጥ ሆና አክስቷም በዶርቲ
መመለስ ደስተኛ መሆኗን እየነገረቻት አለመች፡፡
በነጋታው 3፡00 ሰዓት ላይ
አረንጓዴ ጢማሙ ወታደር ወደ እነርሱ ቀረበ ከአራት ደቂቃ በኃላም ወደ ታላቁ የኦዝ ዙፋን ገቡ፡
ኦዝ ከዚህ በፊት በሰጣቸው ቅደም
ተከተል መሰረት እያንዳንዳቸው እንደሚያዩት ቢጠብቁም በሚያስገርም ሁኔታ በክፍሉ ውስጥ ማንም አልነበረም፡፡
የክፍሉ ኦናነት ከዚህ ቀደም
ኦዝን ካዩበት ሁኔታ ይሄኛው በጣም አስደንጋጭ ሆኖ ስላገኙት እርስ በእርስ ተያይዘው ወደ በሩ ተጠጉ፡፡
በቅርብ ከጉልላቱ በላይ የሚመጣ
የሚመስል የተከበረ እና የረጋ ድምፅ ሰሙ
“እኔ ታላቁና አስፈሪው ኦዝ
ነኝ እነሆ ለምን ትፈልጉኛላችሁ”
ዙሪያ ገባውን በድጋሚ ቃኙት፤
ማንንም ሊያዩ አልቻሉም፡፡
“የት ነው ያለኸው?” ጠየቀች
ዶርቲ
“እኔ በሁሉም ቦታ አለሁ” ሲል
በድምፁ መለሠ፡፡
ነገር ግን ለተራ ሰዎች አይን
አልታይም፡፡ አሁን በዙፋኔ ላይ እቀመጣለሁ፣ ያኔም ልታናግሩኝ ትችላላችሁ፡፡
በእርግጥም ድምፁ ከዙፋኑ የመጣ
ይመስል ነበርና ሁሉም በረድፋቸው ወደዚያው አመሩ
“የመጣነው ቃልህን ትፈፅምልን
ዘንድ ነው ”
“ኦዝ ሆይ”፣አለች ዶርቲ
“ የምን ቃል ” ጠየቀ ኦዝ
“እርጉሟ ጠንቋይ ከሞተች ወደ ካንሳስ እንደምትልከኝ ቃል ገብተህ ነበር
“ አለች ልጃገረዷ
“ለኔ ደግሞ አዕምሮ እንደምትሰጠኝ
ቃል ገብተህ ነበር” አለ ወፍ ማስፈራሪያው
“ለኔም ልብ እንደምትሰጠኝ ቃል
ገብተሀል” አለ እንጨት ፈላጨት ፈላጭ
ፈሪው አንበሳ ደግሞ “ወኔ ልትሰጠኝ
ቃል ገብተሀል” አለው፡፡
እውነት ያቺ እርጉም ጠፍታለችን
? ብሎ ጠየቀ ፤ ዶርቲ ጥያቄው ትንሽ አስፈራት
“አዎን” ፤ “እኔ ነኝ በአንድ
ባልዲ ውሃ ያቀለጥኳት” ብላ መለሰች፡፡
“ወይ ጉድ እንዴት ሊሆን ቻለ
! መልካም ላስብበት ፤ ነገ ወደ እኔ ተመልሳችሁ ኑ”
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ