ከተማና ዩኒቨርሲቲ በአንድ መነፅር









ርእሳችን እንደሚያመለክተው የቅኝታችን ዋነኛ ትኩረት ሁለት መልክ አለው ፤ ይኸውም ሶስት ከተሞችን መነሻ በማድረግ በውስጣቸው የሚገኙትን የከፍተኛ የትምህርት ተቃማትንም አያይዞ በወፍ በረር ለአንባቢዎች ለማስቃኝት ይሞክራል፤ መልካም ንባብ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ክፍል ባዘጋጀው ትምህርታዊ ጉዞ  መነሻ ከሆነችው ሸገር (አቡነ ጴጥሮስ ግቢ) እስከ መዳረሻችን አክሱም ከተማ (ለ1030 ኪሎ ሜትር ርቀት ማለት ነው) ፤ በቆየንባቸው 10 ቀናት  ከሰባት በላይ  ከተሞችንና ሶስት ከፍተኛ የትምህርት ተቓማትን  የማየትና የመጎብኘት አጋጣሚ ተፈጠሮ ነበር፤
እንሆ ቅኝታችን
 ለመግበያ የመረጥናት ደሴ ከተማን ናት ምክንያቱ ደግሞ ከረጅም ጉዞ በኃላ እረፍት ስላደረግንባት ነው፡፡  የጦሳ ተራራ ራሱን አጋልጦ ከተማይቱንና ቆነጃጅቱን ከሌሎች ይደብቅ ይመስል እንደንቁ ሰራዊት ዙሪያዋን ከብባት ይገኛል ፤ደማቅ የንግድ እንቅስቃሴ የሚስተዋልበት የገበያ ስፍራው የጀንበር መጥለቅ ሳያሳስበው  እስከ ምሽት ሸማቾችን በትጋት ያገለግላል ፤ በውስጡ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች፤ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች እንዲሁም የአካባቢው መገለጫ የሆነውና ለተለያዩ ክልሎች በማከፋፈል የሚታወቅበት የእጣን እና የጢሳ ጢስ ዋነኛው ነው፡፡ ከነዚህ ውስጥ  አደስ ፡አሪቲ፡ጉርጉድ ፡አልጋ ነቅንቅ (የጢሱን ሃይለኝነት ለመግለፅ ነው) የመሳሰሉት  በብዛት የሚገኝባት ከተማ ናት፡፡ በልማቱም ረገድ በጥሩ እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች፡፡
የደሴ ከተማ ብቸኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቓም ወሎ ዩኒቨርሲቲ ነው፤ ተቓሙ ከዋነናው ከተማ በስተግራ 2.5 ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ይዘልቃል፤ ይህም ያለው የንግድ እንቅስቃሴን ሁከት የትምህርተ ሂደቱን ሰላማዊ እንዲሆን ረድቶታል፡፡ ምም እንካን ሰፊ ግዛት ቢኖረውም ቅሉ በእንክብካቤና በአግባቡ ባለመያዙ ምክንያት በአካባቢው የሚገኙ የቀንድ ከብቶች ያለ ከልካይ እንዳሻቸው እንዲዘዋወሩ አግዛቸዋል፡፡ በጊቢው ውስጥ ለተማሪዎችት  አገልግሎት የሚሰጡ  ሱቆች፡ ካፌ ፡ ምግብ ቤቶች ወዘተ ይገኙበታል፡፡
           በጣም ሞቃታማ የአየር ጠባይ ኣላት፤ ካየናቸው ከተሞች በንፅህና የመጀመሪያውን ስፍራ ትይዛለች ፤ እንዲሁም መልካም የልማት እንቅስቃሴ የስተዋልባታል፡፡ ሁለተኛዋ ከተማ መቀሌ፤ 3 የሬዲዮ ጣቢያዎች፤ ሁለቱ በአጭር ርቀት በትግርኛ ቃንቓ ሚተላለፉት ድምፅ ወያኔ 102.2 ኤፍኤም ፡ እና መቀሌ ኤፍኤም  104.4  ሲሆኑ ሶስተኛው በመካከለኛ ሞገድ ከፋና ብሮድቻስቲንግ ኮርፖሬት የሚተላለፈው 94.8 ናቸው፡፡ እንዲሁም አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በትግራይ መገናኛ ብዙሃን ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት(ኢቢሲ) ጋር በመተባበር ጠዋት 12፡00 – 3፡00 ፤ ቀትር ላይ 6፡00- 8፡00 እና ምሽት 12፡00- 3፡00 ይተላለፋል ፡፡ በ2001 ዓ.ም በ12 ሰዎች ስራውን የጀመረው በድምፅ ወያኔ ሬዲዮ ነበር፤ አሁን ስራተኛዎቹን ቁጥር ወደ 200 አሳድጋል ፡፡ለተመልካች የሚተላለፉትን  መሰናዶዎች የሚያስተላልፈው ባስገነባው ዘመናዊና ህንፃ ላይ ነው ፡፡ የከተማው የንግድ እንቅስቃሴው ዘርፍ አብዛኛውን የምግብና የመጠጥ ሽያጭ ላይ ያተኩራል፡፡ እንደ አካባቢው ነዋሪዎች ገለፃ ከ80 በመቶ  በላይ የሚሆነው የንግድ ዘርፍ የመጠጥ ሽያጭ ተቆጣጥሮታል፡፡
አምስት የከፍተኛ ተቓማት ያሉዋት መቀሌ  ፤ እንዳሱስ (ዋናው ግቢ) የእንስሳት ትምህርት ክፍል፤ ሃይደር የጤና ሳይንስ ኮሌጅ፤ አሪድ የኮምፒቲሽናል ሣይንስ፤ ኤም አይ ቲ የምንድህስና ኮሌጅ እንዲሁም ለጉብኝት የሄድነው ተማሪዎች ያረፍንበት አዲሃቂ የንግድ ስራ ኮሌጅ  ናቸው፡፡ ወደፊት በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ስም ስድተኛ የትምህርት ተቓም ለመገንባት የክልሉ ትምህርት ቢሮ እቅድ ያመለክታል፡፡በሁሉም የተቁዋማቱ መግቢያ ላይ የሚታየው መልእክት ከሲጋራ ጭስ እና ከሱስ ነፃ ወደሆነው ግቢያችን  እንካን በደህን መጣችሁ የሚለው መልእክት ይቀበሎታል፤ እዚህ ላይ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲዎች አስተዳደር የሚከለው ጥብቅ ቁጥጥር እና ከብክለት ነፃ የሆነ የትምህርት አካባቢን መፍጠር በሁሉም የከፍተኛ ተቓማት ተግባራዊ ቢሆን መልካም ነው፡፡

eliasww@gmail.com

          መዳረሻችን ታሪካዊታና የስልጣኔ ፈር ቀዳጅ እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት መቀመጫ የነበረችው እና ዳግማዊት ኢየሩሳሌም (ምክንያቱም የታቦተ ፅዮን መገኛ በመሆና ) በመባል የምትጠራው አክሱም ከተማ ነች፡፡ ወደ 600 የሚደርሱ ሃውልቶች ይገኙበሰታል፤ ይህም ርዝመቱ 33 ሜትር ክብደቱ ደግሞ 520 ቶን ከሚመዝነው እና የፋሽስት ጦር ለመውሰድ ያልቻለውና ወድቆ ከሚገኘው ጀምሮ በመጠንና በቅርፃቸው የተለያዩ ሀውልቶች ይታያሉ፡ ተምሳሌታቸውም የነገስታትና የመካንንቱ የማቃብር ስፍራዎች መሆናቸው ፤ የቅርፃቸው ቁመታቸው መለያየትም ደግሞ የስልጣን ተዋረድ መኖሩን ያሳየናል፡፡
ሌላው  የንግስት እሌኒ( ሣባ) ቤተ መንግስት ሲሆን ንግስቲቱ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ክፍሎች ለምሳሌ የመታጠቢያ ክፍሎች፤ የመመገቢያ ክፍሎች ፤ የመኝታና ሌሎች ግልጋሎታ ይሰጡ የነበሩ ክፍሎችን ተመልክተናል፡፡ ነገር ግን ለምሰል ማስቀሪያ (ፎቶ ግራፍ ማንሻ ) ተብሎ የተሰረው ስፋራ ወይም እንደ ቆጥ የተሰራው ከፍታ ቢጨምር ለእይታ አመቺና ለምስል ማስቀሪም ተስማሚ ይሆናል ባዮች ነን፡፡
 ሃውልቱን አስቀድሞ የሚገኘውን ቤተ መዘክር  በውስጡ ያሉትን ከአክሱም ስልጣኔ በፊት እና በአክሱም ዘመነ መንግስት ወቅት ይጠቀመሙባቸው የነበሩ ቁሳቁሶች፤ ጌጣጌጦች ፤ የመገበያያ ገንዘቦችና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ በእርግጥ በጥሩ ክብካቤ የተያዙ ቢሆንም ቅሉ ቤተ መዘክር ውስጥ አስጎብኚ ባለመኖሩ ምክንያት አንድ አንድ ማብራሪያ የሚገባቸውን ቅርሶች ለመረዳት አዳጋች አድርጋቸዋል፡፡ 

ርዕሰ አድባራት አክሱም ፅዮን ማርያም ቤተክስትያን ከሃውልቱ ፊት ለፊት ትገኛለች፡ በታሪክ ድረሳናት ላይ እንደምናገኘው የንግስት ሣባ ልጅ ቀዳማዊ ምኒልክ ከኢየሩሳሌም ያመጣት የፅዮን ታቦት መገኛ ገዳም ነው፡፡ ቤተክርስትያኑ በዮዲት ጉዲት ዘመነ መንግስት የቃጠሎ ጉዳት ደርሶበት ነበር ፤ ነገር ግን በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ዘመን አዲስና ዘመናዊ ህንጻ ቤተክርስትያን የተገነባ ሲሆን እስካሁንም አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ለታቦቱም ልዩ የሆነ ጥበቃ እየተደረገለት እንደሚገኝ የተለያዩ መፃህፍት ያስረዳሉ፡፡

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

 ሌላ ሰው….. የሃገራችን የስነ ልቦና መጽሃፍት ጅማሬ

አራቱ መንገደኞች